አህፅሮት ጤፍ በኢትዮጵያ ከሚመረቱ የብርዕና አገዳ ሰብሎች ዋናው ሲሆን በየዓመቱ ቁጥር ከ6.5 ሚሊዮን የማያንስ አርሶ አደር ያመርተዋል፡፡ ይህም አጠቃላይ በብርዕና አገዳ ሰብሎች ከሚሸፈነው ማሳ 30% ድርሻ አለው፡፡ ይሁን እንጂ ከሌሎች ሰብሎች ጋር ሲነፃፀር ምርታማነቱ አነስተኛ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በከፊል አርሶ አደሩ ያልተሻሻሉ የአካባቢ ዝርያዎችን በመጠቀሙና፣ የሰብሉ ተፈጥሯዊ የመጋሸብ ባህሪ ናቸው፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማ በተለየ ምርምር አሰራር የተገኘን የጤፍ ዝርያን በመፈተሸ የተሻለ ምርት፤ የአገዳ ጥንካሬን አንዲሁም የዘር ቀለም ያለውና በአርሶ አደሩ ተመራጭ ዝርያ ማፍለቅ ነበር፡፡ በጥናቱ በቅርቡ የተለቀቀ አንድ ዝርያና አንድ የአካባቢ ዝርያን ጨምሮ 10 የተለያዩ የጤፍ አይነቴዎችን በማካተት በስድስት ወካይ ጤፍ አብቃይ ቦታዎች ላይ ተፈትሸው ተስፋ (ደዘ-ክሮስ-457) ተብሎ የተሰየመውና የተለያዩ የጤፍ አይነቴዎች ተዳቅለው የተገኘው ዝርያ ከሌሎች ማወዳደሪያ ተፈታሽ ዝርያዎች የተሻለ ውጤት በማስመዝገቡ በብሄራዊ የዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ ተገምግሞ ለምርት እንዲለቀቅ ተወስኗል፡፡ ይህ ዝርያ ከሌሎች ዝርያዎች በንፅፅር መጋሸብን በመቋቋሙ፤ የተሻለ ምርት በመስጠቱ በአርሶአደሩ ተፈላጊ ከመሆኑም በሻገር ከዝርያው ባህሪ የተነሳ ለመስኖ እርሻና በሰብል መድረሻ ጊዜ የማጨጃ ...